fbpx

Leave Your Immigration Worries In Our Hands

  1. Home
  2.  » Amharic

Office & Staff

የኢሚግሬሽን ሕግ ጠበቃ የሚ ጌታቸውና ባልደረቦችዋ

ከ21 ዓመት በላይ በከፍተኛ ችሎታ ፍጹም ርህራሄ በተሞላበት አቀባባል የጥብቅና አገልግሎት ስንሰጥ ቆይተናል

 

የየሚ ጌታቸው የኢሚግሬሽን ሕግ ቢሮ የአሜሪካ የኢሚግሬሽን ሕጎች ምን ያህል ውስብስብና የሚያጨናንቁ ሊሆኑ እንደሚችሉ በደንብ ያውቃል፡፡ አገልግሎት እየሰጠን በቆየንባቸው በእነዚያ በርካታ ዓመታት ውስጥ ተቋማችን ምቹ እና እንክን የለሽ በሆነ መልኩ በመላው ዓለም የሚገኙ አመልካቾች አሜሪካን አገር ለመኖር የሚያስችላቸውን ሁኔታ በማስተካከል ሲረዳ ቆይቷል፡፡ ከመካከለኛው ምስራቅ፣ ከአፍሪካ፣ ከአውሮፓ፣ ከአውስትራሊያ፣ ከመካከለኛውና ከደቡብ አሜሪካ እንዲሁም ከእሲያ የመጡ ደንበኞቻችንን በሚገባ አስተናግደናል፡፡ ለማንኛውም ጉዳይ ስኬታማነት ቁልፉ ነገር የተደረገው የዝግጅት መጠን ነው፡፡ በተቋማችን ለሚያዘው እያንዳንዱ የሕግ ጉዳይ የምንጠቀመው አካሄድ ጥልቅና ባለብዙ ገጽታ ነው፡፡ የአገር ሁኔታን የሚመለከት ሰፊ ጥናት (ምርምር) ከማካሄድ ጀምሮ የተገኙ ፍሬ ነገሮችን እና የሕግ ትግበራን በሚመለከት ዝርዝር ግምገማ እስከማድረግ ድርስ የምንሄድ ሲሆን የደንበኛችንን ጥቅም ለማስጠበቅ ከዚያም በላይ በመሄድ የማንፈነቅለው ድንጋይ አይኖርም፡፡ ጉዳይዎትን ተማምነው በእኛ ላይ ሲጥሉት እኛም ይህን እንደ ትልቅ አደራ ከመውሰዳችን በተጨማሪ ጉዳዮ በባለሙያ እንደተያዘና የሚቻለው ነገር ሁሉ እየተደረገ መሆኑን ቅድሚያ የምንሰጠው የሥራ ጉዳያችን ይሆናል፡፡ ከመላው ዓለም ለሚመጡ አመልካቾች ጥብቅና የምንቆም ኃይለኛ የሕግ ተከራካሪዎች ነን የአሜሪካ ዜጋ ወይም ሕጋዊ ቋሚ ነዋሪ በሆኑ ዘመዶችዎ በኩል የሚደረግ የድጋፍ ተጠሪነት (sponsorship) ሂደትን፣ በአሜሪካ የፖለቲካ ጥገኝነት የማግኘት ጥያቄን፣ የዜግነት ወረቀቶችን ለራስዎም ሆነ ለቤተሰብዎ ማግኘትን፣ውጤታማ የሆነ ከአገር ማባረርን መከላከያ (removal defense) ስልት መንደፍን፣ ወይም በመጋፈጥ ላይ ያሉትን ማንኛውንም የሕግ ጉዳይ በሚመለከት በትጋት የሚሰራው የሕግ ቡድናችን እርስዎን ወደ ፈለግት መፍትሔ ሕጉ በሚፈቅደው መንገድ ሊረዳዎ ዝግጁ ነው፡፡ ተቋማችን እርስዎን እንዴት ሊረዳዎት እንደሚችል ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎችን ለማግኘት በድረ ገጹ መጀመሪያ ላይ በመሔድ ስልክ (408) 292-7995 ወይንም ኢሜል yemi@ethiopianattorney.com ያድርጉልን የመስሪያ ቤቱ አጠቃላይ ገጽታ የተረጋገጠ ውጤት ያስመዘገበች በታማኝነት የምታገለግል የሳን ሆዜ የኢሚግሬሽን ጠበቃ ቢሮአችንን ከከፈትንበት ከ1988 (እ.ኤ.አ. ከ1996) ዓ.ም. ጀምሮ እውቀትና ልምድ ያካበተችው ጠበቃችን እና ሠራተኞቻችን በሺዎች የሚቆጠሩ ግለሰቦች እና ቤተሰቦች የኢሚግሬሽን እንቅፋቶቻቸውን አሸንፈው ስኬታማ እንዲሆኑ ረድተዋል፡፡ በአገራቸው የተፈጸመባቸውን ማሳደድ በመሸሽ ጥገኝነት የሚጠይቁ ግለሰቦችንም ሆነ የተማሪ ቪዛ ወይም ቋሚም ይሁን ጊዜያዊ የሥራ እድሎችን ለማግኘት የሚጥሩ ግለሰቦችን እንዲሁም ከአገር በማባረር/በማስወጣት (removal/deportation) ሂደት ላይ እንዲሆኑ ተደርገው አሜሪካ ውስጥ ለመቆየት በመታገል ላይ ያሉ ግለሰቦችን ወይም የአሜሪካ ዜጋ እና ሕጋዊ ቋሚ ነዋሪ (ባለ አረንጓዴ ካርድ) የሆኑ ሰዎች ዘመዶች ስለመሆናቸው ማመልከቻ የቀረበባቸው ቤተሰቦችን ጨምሮ- የሕግ ቢሮአችን በርህራሄ እና በከፍተኛ ችሎታ ስደተኞችን በታማኝነት ያገለግላል፡፡ በማህበረሰባችን ውስጥ ደንበኞቻችንን ወክለን ለእነርሱ በመታገል መልካም ስም ገንብተናል፡፡ ከአፍሪካ፣ ከመካከለኛው ምስራቅ፣ ከመካከለኛው እና ከደቡብ አሜሪካ፣ ከአውሮፓ፣ ከእስያ እና ከአውስትራሊያ የመጡ ደንበኞቻችን ጋር በመሥራት ያካበትነው ልምድ ደንበኞቻችንን ለማስተናገድ የሚያስፈልጉትን በቀላሉ የማይታዩ የትርጉም ወይም የአገላለጽ ልዩነቶችን (nuances) እና ስሜት መጠበቅን (sensitivity) እንድንለማምድ አግዞናል፡፡ አሰራራችን ማንኛውንም ጉዳይ ከመያዛችን በፊት ወዳጃዊ የሆኑ የየሚ ጌታቸው የኢሚግሬሽን ሕግ ቢሮ ሠራተኞች የምክር አገልግሎት የሚሰጥበት ቀጠሮ ይይዙልዎታል፡፡ በቀጠሮውም የሳን ሆዜ የኢሚግሬሽን ጠበቃችን ጊዜ ወስዳ እርስዎን ታናግርዎታለች፣ ፍላጎቶችዎን ታዳምጣለች፣ ሰነዶችዎትን ትመረምራለች፣ ሁሉንም ጥያቄዎችዎትን ትመልሳለች እንዲሁም ያሉበትን የግል ልዩ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት ያጋጠመዎትን የኢሚግሬሽን ችግር ለማሸነፍ ያሉትን ከሁሉም የተሻሉ አማራጮች ታብራራልዎታለች፡፡ ለምክር አገልግሎት $260 የአሜሪካ ዶላር የምናስከፍል ሲሆን  ግልጽ እና ትክክለኛ መረጃን በሚገባ መልኩ መስጠት ስኬታማ ውጤት ለማምጣት የመጀመሪያውና እጅግ ጠቃሚ የሆነው እርምጃ መሆኑን እናምናለን፡፡ የመስሪያ ቤታችን ባልደረቦችን ተዋወቁ የሚ ጌታቸው-ዋና ጠበቃ የሚ ጌታቸው ተወልዳ ያደገችው አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ ነው፡፡ ራሷ ስደተኛ በመሆኗ ውስብስብ ሂደቶችን ከሁለቱም አቅጣጫ ትረዳቸዋለች፡- እንደ ስደተኛ እና እንደ ጠበቃ፡፡ ሥራዋን በሁለት ቁልፍ ምሰሶዎች ገንብታለች፡- ርህራሄ እና ከፍተኛ ችሎታ፡፡ በእነዚህ ምሰሶዎች በመመራት በሺዎች የሚቆጠሩ ከአፍሪካ፣ ከመካከለኛው ምስራቅ፣ ከመካከለኛው እና ከደቡብ አሜሪካ፣ ከአውሮፓ፣ ከእስያ እና ከአውስትራሊያ የመጡ ግለሰቦች እና ቤተሰቦች በስኬታማነት ሰፊ የሆኑ የተለያዩ የኢሚግሬሽን እንቅፋቶችን እንዲያሸንፉ ረድታለች፡፡ የሚ ያደገችው በኢትዮጵያ ሲሆን ጨካኝ የኮሚዩኒስት ወታደራዊ መንግስት በስልጣን ላይ በነበረበት ጊዜ ነበር፡፡ ራሷ የሰብአዊ መብት መደፈሮች human rights indignations ያጋጠሟት ሲሆን በአካባቢዋ በሰፊው ለተካሄደው ማሳደድም የአይን እማኝ ናት፡፡ በእነዚያ ፈታኝ ጊዜዎች የተገነዘበችው ነገር ሕጎች ቢኖሩም እንኳን ለሕጎቹ ማስፈጸሚያ የሚሆኑ የዳኝነት አሰራር ሂደቶች ባለመኖራቸው ምክንያት ሕብረተሰቡ በሕጎቹ ለመገዛት ፈቃደኛ እንዳይሆን የሚያደርግ ውጤት ማሰከተሉን ነው፡፡ ከዚህ በመነሳት ነው የሚ ተጋላጮች ተገቢ የሕግ ከለላ የማግኘት መብቶቻቸው (due process rights) እንዲከበሩላቸው ለማድረግ ኃይለኛ ተሟጋች ለመሆን የወሰነችው፡፡ ወደ አሜሪካ ከመሰደዷ እና የራሷን የኢሚግሬሽን ሕግ አገልግሎት መስጫ ከመጀመሯ በፊት የሚ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተመርቃ ነበር፡፡ በ1988 (እ.ኤ.አ. በ1996) በሳን ሆዜ፣ ካሊፎርኒያ ውስጥ የኢሚግሬሽን ሕግ አገልግሎት መስጠት ጀመረች፤ በአለማችን ዙሪያ ያሉ ስደተኞችን ከጥገኝነት፣ ከአገር ማባረርን ከመከላከል፣ ቤተሰብ ላይ ከተመሰረተ ኢሚግሬሽን፣ ከቀሪ ማስደረጊያዎች (waivers)፣ ከዜግነት እና ዜግነት ከማግኘት ጋር የተያያዙ ሂደቶች በጠበቃነት ወክላለች፡፡ በአሁኑ ጊዜ የሚ የአሜሪካ የኢሚግሬሽን ጠበቃዎች ማህበር ሳንታ ክላራ የ2017-2018 ሊቀ መንበር ስትሆን ባለፉት ሶስት ዓመታት በተለያዩ ደረጃዎች የአስፈጻሚ ኮሚቴው አካል ሆና ቆይታለች፡፡ በተጨማሪም ከአገር ማባረርን (removal) መከላከልን በሚመለከት (Asian Law Alliance) በአማካሪነት እና በምክር ጠቋሚነት (Mentor) በማገልገል ላይ ትገኛለች፡፡ የሚ የሥራ ባልደረባዎቿ በኢሚግሬሽን ሕግ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ልቀው እንዲገኙ የምትገፋፋ በመሆኑ ብዙ ጊዜ እንደ አነቃቂ ተደርጋ ትገለጻለች፡፡ ፍትሕ አናሳ አቅም ላላቸው ሰዎች ተደራሽ እንዲሆን ለማድረግ አንዳችም እድል የማያመልጣት ከመሆኑ የተነሳ በነፃ ለሚሰጡ አገልግሎቶች በታታሪነት የምትጋደል ናት፡፡ በተለይም በዲሊ፣ ቴክሳስ በሚገኘው የካራ ነፃ የሕግ አገልግሎት ፕሮጀክት (Cara Pro Bono Project) ላይ ለብዙ ጊዜ ስታገለግል ቆይታለች፤ በየዓመቱ በሚከናወነው የጠበቆች ማህበር የበጎ ፈቃደኛ ክሊኒኮች ውስጥ ለሰባት ዓመታት የበጎ ፈቃደኝነት አገልግሎት ሰጥታለች፤በቤተ ክርስቲያኖች እና በቤተ መቅደሶች መብቶቻችሁን እወቁ በሚል አዘውትራ ንግግር ታደርጋለች፤ ለሌሎች የኢሚግሬሽን ጠበቃዎች በተደጋጋሚ የነፃ የሕግ አገልግሎቶችን መርታለች፤ በግሏ በመቶዎች የሚቆጠሩ በችግር ላይ የነበሩ ግለሰቦችን በጥብቅና ወክላለች፡፡ ከኢሚግሬሽን ሕግ ባሻገር በአሜሪካ ውስጥ በሚገኙ የስደተኛ ሕብረተሰቦች ዘንድ እጅግ ተፈላጊነት ያላት ለወጣቶች እና ለታዳጊዎች መንፈስ አነሳሽ ተናጋሪ (motivational speaker) ናት፡፡ ከዚህም ሌላ ስኬታማ ባለሙያዎች ለመሆን ለሚጥሩ ስደተኛ ተማሪዎች ምክር ጠቋሚ (mentor) በመሆን በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዓቶቿን ለበጎ ፈቃደኝነት አገልግሎት ስታውል ቆይታለች፡፡ የሚ በኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ውስጥ ደግሞ በአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ የአማርኛ መርሃ ግብር ላይ ወቅታዊ የኢሚግሬሽን ጉዳዮችን በሚመለከት ለበርካታ ጊዜዎች ቃለ መጠይቆች ተደርገውላታል፡፡ የሚ ከሕግ ዲግሪዋ በተጨማሪ በጋብቻ እና ቤተሰብ ሕክምና (Therapy) የማስተርስ ዲግሪ አላት፡፡ በዌስተርን ሴሚነሪ ውስጥም በሕግ እና በስነ ምግባር ጉዳዮች በተጨማሪ (Adjunct) ፕሮፌሰርነት አገልግላለች፡፡ ስለ የሚ እና ስለ ቀሪዎቹ የየሚ ጌታቸው የኢሚግሬሽን ቢሮ ቡድን አባሎቻችን ተጨማሪ ለማወቅ እባክዎን (408) 292-7995 ላይ ይደዉሉልን፡፡ ሜድያ አጋንሳሪ ናስራባዲ-ተባባሪ ጠበቃ ተቋማችንን የተቀላቀለችው በ2010 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. በ2018) ነው፡፡ የማሳቹሴትስ ግዛት ኒው ኢንግላንድ ሎው ኦፍ ቦስተን  ዩኒቨርሲቲ የ2009 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. የ2017) የህግ ተመራቂ ስትሆን የጥብቅና ፈቃድ በማሳቹሴትስ አግኝታለች፡፡ ተወልዳ ያደገችው  ኢራን ሀገር ሲሆን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን እና የህግ ትምህርቷን በአሜሪካን ሀገር ተከታትላለች :: ወደ እኛ ቢሮ ከመምጣቷ በፊት ካራ ፕሮ ቦኖ ነፃ የሕግ አገልግሎትፕሮጀክት (Cara Pro Bono Project)  እና ሜርሴድ ፐብሊክ ዲፌንደር ቢሮ (Merced Public Defenders Office) በሚባሉ ድርጅቶች ውስጥ ሰርታለች::ሜድያ  የፋርሲ ቋንቋ ትናገራለች::ሄለን ተሰማ-የቢሮ አስተዳዳሪ የቢሮ አስተዳዳሪያችን የሆነችውን ሄለን ተሰማን ያግኟት፡፡ በአየር መንገድ ኢንዱስትሪ ውስጥ በደንበኞች አገልግሎት ሰፊ የሥራ ልምድ ይዛ መጥታለች፡፡ በተለያዩ መንገዶች የቢሮአችን ሥራ እንዲካሄድ ታደርጋለች፤ በተለይም ወግ አዋቂነቷ ሁልጊዜም እንድንስቅ ያደርገናል፡፡